ኑር የቁርዐን ባንክ

እንኳን ወደ ኑር የቁርኣን ባንክ መጡ!

መልዕክተኛውም ”ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት” አለ
አል ፉርቃን – 30

ስኬቶቻችን!

ድርጅታችን በህግ አግባብ ከተቋቋመበት ግዜ ኣንስቶ ባለፉት 15 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የቁርአን እጥረት በተስተዋለባቸው የኢትዮጵያ የገጠር ክፍሎች በመዟዟር እስከአሁን ከ100 ሺ በላይ የቁርኣን ኮፒዎችን በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ማሰራጨት ችሏል ።

ኑር የቁርዐን ባንክ

ቁርኣን ለሁሉም

ኑር የቁርዐን ባንክ

ቁርኣን ስርጭት

አላማችን

የቁርኣን ኮፒዎችን ከማዳረስ ጎን ለጎን አማኙ የማህበረሰብ ክፍል ከቁርአን ጋር ያለውን ቀረቤታ የሚያጠነክርበትን ጠንካራ መሰረት የመጣል ፣ ቁርኣንን የሚያስተምራቸው ኡስታዝ በማጣት እእንዲሁም ከዕለት ጉርስ የኑሮ ጥያቄና ሩጫ ብዛት ከቁርአን ጋር የተረሳሱ ወገኖች ዳግም የቁርአንን ብርሃን የሚያገኙበትን ድልድይ የመገንባት እና ከሙስሊሙ ውጪ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ቁርአን የተላከው ለእነርሱም ጭምር እንደሆነ በማስረዳት ለአስተምሮቱ መንገድ የመጥረግ እና የማመቻቸት ስራዎችን ለመስራት ዘርፈ ብዙ ዕቅዶችን ቀርጿ በመስራት ላይ እንገኛለን። 

ግባችን

ኑር የቁርአን ባንክ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ሚያዚያ ወር 2013 ዓ/ል ዋና መቀመጫውን አዲስ አበባ ላይ በማድረግ የቁርአን ኮፒዎችን በመላው ኢትዮጵያ የገጠር ክፍሎች የማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማራ ህጋዊ ባንክ ነው ። ባንኩ ከቁርአን ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከተመሰረተ በአጭር ግዜ ውስጥ በማህበረሰቡ ዘንድ ይህ ነው የማይባሉ ክፍተቶችን በመሙላት ከፍተኛ እምነትና ተቀባይነትን አግኝቷል ። በተጨማሪም ከሀይማኖቱ የእምነት አባቶች ፣ መሻኢኾች ፣ ዲኘሎማቶችና ዱአቶች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ እና አድናቆትን ማግኘት ችሏል።

ኑር የቁርዐን ባንክ
Play Video about ኑር የቁርዐን ባንክ

ለኑር የቁርኣን ባንክ

ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው የበጎ አድርጎት አስተዋፅዖ በዛሬው ዕለት ከባቡል ኸይር ዋና ስራ አስኪያጅ ከሆኑት ወ/ሮ ሀናን ማህሙድ እጅ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል !

jummah mubarek!

ዳቡስ_አትንባቆ ወቅቱ የሌሊት ነው ሰአቱ 9:30 ። ከታች በምስሉ የምትመለኩት የሂላል መስጂድ ቅጥር ግቢ ሲሆን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዞን ዳቡስ አትንባቆ …

ወቅቱ የሌሊት ነው ሰአቱ 9:30 ። ከታች በምስሉ የምትመለከቱት የሂላል መስጂድ ቅጥር ግቢ ሲሆን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዞን ዳቡስ አትንባቆ ቀበሌ …

የ500ሺቁርኣን_ዘመቻ ኑር የቁርኣን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በዘንድሮ ረመዳን ባዘጋጀው 500ሺ ቁርኣኖችን የማሰባሰብ መርሃግብር …