በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ላሉ የገጠር መንደሮች የሙስሃፍ ስርጭት አከናውኗል ።

በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ላሉ የገጠር መንደሮች የሙስሃፍ ስርጭት አከናውኗል ።
ኑር ቁርዓን ባንክ ከድሬዳዋ የቁርአን ዘማቾች ጀመዓ ጋር በመተባበር ከከተማዋ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዋሂል ወረዳ ‘ዳሩል ሀዲስ’ መድረሳ በመገኘት በ2 ፈረቃ ለሚቀሩ 1600 ህፃናትና ደረሶች 1000 ኑራኒያ ፣ 90 ያህል ባለ 8 ጁዝ ሙስሃፍና 800 ያህል 30 ጁዝ የቁርአን ኮፒዎችን አድርሷል ።
የዳሩል ሀዲስ መድረሳ አስቀሪ የሆኑት ኡስታዝ በያን የተማሪዎቻቸው የሙስሃፍ ችግር በመቀረፉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ፣ መንፈስን በሚያድስ የህፃናቶቹ የቁርአን ዜማ አሰምተውን ለኑር ቁርአን ቤተሰቦችና ለቁርኣን ዘማቾች ጀመዓ ዱአ በማድረግ ሙስሃፎቹን ተረክበዋል ።

4 thoughts on “በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ላሉ የገጠር መንደሮች የሙስሃፍ ስርጭት አከናውኗል ።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *