ኑር የቁርኣን ባንክ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ቅርጫፍ መስሪያ ቤቱን እነሆ በይፋ ከፈተ !

ኑር የቁርኣን ባንክ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ቅርጫፍ መስሪያ ቤቱን እነሆ በይፋ ከፈተ !
ኑር የቁርኣን ባንክ ‘ቁርኣን ለሁሉም’ በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ ከተማና የገጠር ክፍሎች የሙስሃፍ እጥረትን ለመቅረፍ የተቋቋመ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አሁን ድረስ በመላው የሀገሪቱ የገጠር መንደሮች መስጂዶችና ሀሪማዎችን በመጎብኘት ከ95ሺ በላይ የቁርኣን ኮፒዎችን አሰራጭቷል ።
ከቁርኣን ስርጭት ጎንለጎን ከአጋር ተቋማቶች ጋር በመተባበር በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችንም በመከወን ይታወቃል ።
ባሳለፍነው ሳምንት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ላይ ሁለተኛ የቅርጫፍ መስሪያ ቤቱን በይፋ የከፈተው ኑር የቁርኣን ባንክ
በቅርንጫፍ ማዕከሉ የተሰበሰቡ በርካታ የቁርኣን ኮፒዎችን በመውሰድ በድሬዳዋና ሐረሪ ገጠራማ ክፍሎች ለሚገኙ ጥንታዊ መሳጂዶችና ሀሪማዎች ሙስሃፎቹን ማሰራጨት ችሏል ።
ሐረር ውስጥ ሱቅጣጥ በሪ ፈረጀት ኢብራሂም መስጂድ በመገኘት ለ 80 ተማሪዎች የሚሆኑ ሙስሃፎችን በኡስታዛቸው ሙጂቡራህማን አማካኝነት ማስረከባችንን እየገለፅን ፤ ሐረር ውስጥ ባቢሌ ፋብሪካ አካባቢ ለሚገኘውም አው ሙጃሂድ መድረሳ ለ650 ተማሪዎች የሚሆኑ ሙስሃፎችን አስረክበናል ።
በተጨማሪም ሐረር ቀበሌ 13 አካባቢ በሚገኘው አዲሱ የ ጀሚየተል ቁርኣን ተህፊዝ ማዕከል በመገኘት እየተቋቋመ ለሚገኘው ሰፊ ማዕከል የቁርኣን ኮፒዎችን ሰጥቷል ።
ቀጥሎም በድሬዳዋ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው መናፈሻ አንጀሎ መንደር በመገኘት አቡበክር መስጂድ ውስጥ በሁለት ፈረቃ ቂርአታቸውን ለሚከታተሉ ከ250 በላይ ለሚሆኑ እናቶች ደረሶችና ህፃናት 300 የቁርአን ኮፒዎች አስረክቧል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *