ኑር የቁርዓን ባንክ በዛሬው ዕለት በታሪካዊቷ ሀረር ከተማ

ኑር የቁርዓን ባንክ በዛሬው ዕለት በታሪካዊቷ ሀረር ከተማ በመገኘት በሀረሪ ቅርብ ርቀት ውስጥ በሚገኙና ከ1000ሺ አመት በላይ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጡ በቆዩ ጥንታዊ መሳጂዶችና ሀሪማዋችን በመዘየር የሙስሃፍ ስርጭት አከናውኗል ።
ኑር ቁርዓን ባንክ የሀረሪ ተወላጅ ከሆኑት ወንድም አቡ ሙሀመድ እና ወንድም ሙኒብ የኑስ ጋር በመተባበር ከሀረር ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኙ ጥንታዊ መሳጂዶች ውስጥ መስጂደል ኢመርዲን ፣ ኡጋዝ ፣ አይነፊሳ እና ኮረሜ በመገኘት ለመስጂዱ ኢማሞች እና ኡስታዞች በአጠቃላይ 1200 የቁርአን ኮፒዎችን ማድረስ ችሏል ።
የአካባቢው ኡስታዞችና የመስጂድ ኢማሞች በበኩላቸው አሁን ላይ በፈረቃ ወንድ እና ሴት ተማሪዎች እንዲሁም እናቶችና አባቶችን በቋሚነት እያስቀሩ መሆኑን ገልፀው በከፍተኛ ሁኔታ የሙስሀፍ እጥረት በመኖሩ ሁሉንም ደረሶች በተመቻቸ ሁኔታ ለማስቀራት እንደተቸገሩም ነግረውናል ። አያይዘውም ኑር የቁርዓን ባንክ በጊዜያዊነት ያለባቸውን የሙስሃፍ እጥረት በመሸፈኑ ደስታቸውን የገለፁ ሲሆን ሙስሃፎቹን ተረክበው ደስታቸውን በዱአ ገልፀውልናል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *