መስጂዱ በዋነኝነት በዲመካ ነዋሪዎች ጀመአ አስተባባሪነት የተሰራ ሲሆን ኑር የቁርኣን ባንክም ሙሉ የመስጂድ ምንጣፍ ፣ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ግብዓት የሚውል የሶላር ሲስተም ፣ የድምፅ ማጉያ (ማይክራፎን) እና አቅመ ደካማ ለሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች በርካታ አልባሳቶችን በስጦታ መልክ በማበርከት በጋራ የ ‘ሆር አል ነጃሺ’ን መስጂድ አስመርቋል ።
በዕለቱም ታላላቅ የጎሳው አባቶች ፣ የሐመር ወረዳ አስተዳደሮች ፣ የተጎራባች ወረዳ (የበና ፀማይ የማህበረሰብ ክፍሎች) እና የኤርቦሬ ከተማ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ኘሮግራሙ ባመረና በደመቀ መልኩ ተሰናድቶ ቀርቧል ። በመጨረሻም በዕለቱ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን ሸሀዳ የማሲያዝ ኘሮግራም ተካሂዷል ።
ውድ የኑር ቁርኣን ባንክ ደጋፊ ቤተሰቦች እነሆ በእናንተ የላቀ እገዛና ትብብር በሀገራችን ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫዎች የታላቁ ጌታችን የአላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ቃል የሆነውን ‘ቁርኣን’ ከማዳረስ ጎን ለጎን ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በመስራት በአላህ ፍቃድ ውጤታማ ሆነናል ፤ ስለሆነም ከምንሰራው በላይ ለመስራት የዘወትር ድጋፋችሁ ምክርና ዱዓችሁ አይለየን ።
ዩ ትዩብ ቻነላችንን subscribe ያድርጉ👉 https://youtu.be/hT5t7nKyOj4
ቴሌግራም ቻናላችን 👉 http://t.me/NurQuranBank።
Website:- https://nurquranbank.org/
በአካል_ለመምጣት
ፒያሳ በኒ መስጅድ ሱማሌተራ የገበያ ማዕከል 8ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 830 ያገኙናል
ለበለጠ_መረጃ
0929501670 ወይም 0911285537
ኑር የቁርዓን ባንክ Nur Quran Bank