ስለ እኛ

ድርጅታችን ኑር የቁርአን ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙስሀፎችን ለማሰራጨት ብሎም ከቁርአን ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ለመከወን የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ተቋም ነው።

ኑር የቁርዐን ባንክ፦

ድርጅታችን ኑር የቁርአንን ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙስሀፎችን ለማሰራጨት ብሎም ከቁርአን ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ለመከወን የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ተቋም ሲሆን በኢትዮጵያ ፌ/ዲ/ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣናት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ ቁጥር 6229 ልዩ የሙያ ፍቃድ እና እውቅና ያገኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ተቋም ነው ።

ድርጅታችን በህግ አግባብ ከተቋቋመበት ግዜ ኣንስቶ ባለፉት 15 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የቁርአን እጥረት በተስተዋለባቸው የኢትዮጵያ የገጠር ክፍሎች በመዟዟር እስከአሁን ከ95 ሺ በላይ የቁርኣን ኮፒዎችን በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ማሰራጨት ችሏል ። ከተመሰረተ በአጭር ግዜ ውስጥ በማህበረሰቡ ዘንድ ይህ ነው የማይባሉ ክፍተቶችን በመሙላት ከጥንታዊ መሳጂዶች መድረሳና ሀሪማዎች ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የቁርዓን ማስተማሪያ ዛውያዎችን ፣ ሀሪማና መድረሳዎችን በመደገፍ በተለያዩ ግዜያት ለአካባቢው ነዋሪዎች የአልባሳት የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ።

ኑር የቁርአን ባንክ የተመሰረተበት ዋና ዋና ዓላማ እና ግቦች፡-

ኑር የቁርአን ባንክ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ሚያዚያ ወር 2013 ዓ/ል ዋና መቀመጫውን አዲስ አበባ ላይ በማድረግ የቁርአን ኮፒዎችን በመላው ኢትዮጵያ የገጠር ክፍሎች የማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማራ ህጋዊ ባንክ ነው ። ባንኩ ከቁርአን ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከተመሰረተ በአጭር ግዜ ውስጥ በማህበረሰቡ ዘንድ ይህ ነው የማይባሉ ክፍተቶችን በመሙላት ከፍተኛ እምነትና ተቀባይነትን አግኝቷል ። በተጨማሪም ከሀይማኖቱ የእምነት አባቶች ፣ መሻኢኾች ፣ ዲኘሎማቶችና ዱአቶች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ እና አድናቆትን ማግኘት ችሏል።

ኑር የቁርአን ባንክ በይፉ ስራ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቁርአን እጥረት ኣለ ወይ ? የሚል መሰረታዊ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ከቁርኣን እጥረት ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ ጥናቶችን በሀገሪቱ ክልል ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎችን በመዟዟር ከጥንታዊ መሳጂዶች መድረሳና ሀሪማዎች ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የቁርዓን ማስተማሪያ ዛውያዎችን በመጎብኘት በተጨባጭ የቁርአን ኮፒዎች እጥረት ምን ድረስ እንደሆነ የሚያሳዩ ጥናቶችን ሰርቷል።

በአንፃሩ የቁርኣን ኮፒዎችን ከማዳረስ ጎን ለጎን አማኙ የማህበረሰብ ክፍል ከቁርአን ጋር ያለውን ቀረቤታ የሚያጠነክርበትን ጠንካራ መሰረት የመጣል ፣ ቁርኣንን የሚያስተምራቸው ኡስታዝ በማጣት እእንዲሁም ከዕለት ጉርስ የኑሮ ጥያቄና ሩጫ ብዛት ከቁርአን ጋር የተረሳሱ ወገኖች ዳግም የቁርአንን ብርሃን የሚያገኙበትን ድልድይ የመገንባት እና ከሙስሊሙ ውጪ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ቁርአን የተላከው ለእነርሱም ጭምር እንደሆነ በማስረዳት ለአስተምሮቱ መንገድ የመጥረግ እና የማመቻቸት ስራዎችን ለመስራት ዘርፈ ብዙ ዕቅዶችን ቀርጿ በመስራት ላይ ይገኛል።

"ሙሃመድ ሆይ!"

“መወሳትን ላንተ ከፍ አድርገንልሃል”

"ሙሃመድ ሆይ!"

ለአለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም።

ተልዕኮዐችን

የማህበረሰብ ክፍል ከቁርአን ጋር ያለውን ቀረቤታ የሚያጠነክርበትን ጠንካራ መሰረት የመጣል ፣ ቁርኣንን የሚያስተምራቸው ኡስታዝ በማጣት እእንዲሁም ከዕለት ጉርስ የኑሮ ጥያቄና ሩጫ ብዛት ከቁርአን ጋር የተረሳሱ ወገኖች ዳግም የቁርአንን ብርሃን የሚያገኙበትን ድልድይ የመገንባት እና ከሙስሊሙ ውጪ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ቁርአን የተላከው ለእነርሱም ጭምር እንደሆነ በማስረዳት ለአስተምሮቱ መንገድ የመጥረግ እና የማመቻቸት ስራዎችን ለመስራት ዘርፈ ብዙ ዕቅዶችን ቀርጿ በመስራት ላይ ይገኛል።

ኑር የቁርዐን ባንክ

ኑር የቁርዐን ባንክ በድሬዳዋ

ኑር የቁርዐን ባንክ

ኑር የቁርዐን ባንክ በሃረር

ኑር የቁርዐን ባንክ

ኑር የቁርዐን ባንክ በባሌ

ኑር የቁርዐን ባንክ

ኑር የቁርዐን ባንክ በደቡብ ኦሞ ሃመር

ኑር የቁርዐን ባንክን ይደግፉ