ኑር የቁርኣን ባንክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የገጠመው ድንቅ ክስተት
ወቅቱ የሌሊት ነው ሰአቱ 9:30 ። ከታች በምስሉ የምትመለከቱት የሂላል መስጂድ ቅጥር ግቢ ሲሆን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዞን ዳቡስ አትንባቆ ቀበሌ ውስጥ ተገኝተናል ። ከቦታው እንደደረስን ውዱእ ለማድረግ ውሃ መፈለግ ጀመርን ። ‘በቂ የሚባል ባይሆንም እንግዶች ስለሆናችሁ ለእናንተ ብለን ከሩቅ ቦታ ያመጣናት ውሃ አለች’ ብለው ጥቂት የውዱእ ውሃ ሰጡን ። እግረ መንገድ አካባቢው ላይ …